በኢትዮጵያ አማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ባለው የትጥቅ ግጭት፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ወታደሮች በባህር ዳር ከተማ ስድስት ሰላማዊ ሰዎችን ከህግ አግባብ ውጪ ገድለዋል። በዚህ አጭር ምርመራ ሪፖርት አምነስቲ ኢንተርንሽናል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም እንዲሁም መንግስት አፋጣኝ ምርመራ እንዲያደርግ እና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ አሳስቧል።

