ኢትዮጵያ: “ለአባቴ የሞት ፍርድ” በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሜታ ያደረገው አስተዋጽኦ

በህዳር ወር በ2013 ዓ.ም፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እጅግ አሰቃቂ ጦርነት ተቀሰቀሰ። በ2013 ዓ.ም የመረጃ መንታፊዋ ፍራንሲስ ሃውገን እንደተናገረችው፣ ፌስቡክ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፣ “ የጎሳ ግጭትን እንዲቀጣጣል” አድርጓል። ይህ ዘገባ፣ ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ በትግራይ ማህበረሰብ ላይ በተፈጸመው ከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ የሜታ ሚና ምን እንደነበረ የፈተሸ ጥናት ነው። በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተሳትፎ ላይ የተመረኮዘ የንግድ ሞዴል፣ በኢትዮጵያ የትጥቅ ግጭት ወቅት ያሳደረውን አስከፊ ተጽእኖ ሪፖርቱ ያሳያል። ምንም እንኳን ኩባንያው በ2009 ዓ.ም፣ ሮሂንጃዎች ላይ ለደረሰው ግፍ መባባስ ካደረገው አስተዋፅኦ ትምሀርት ወስጃለሁ ቢልም፣ እየተከተለው ባለው አሰራር የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥም በድጋሚ ተመሳሳይ ጉዳቶች እንዳደረሰ ጥናቱ አሳይቷል።.

Choose a language to view report

Download PDF